አጭር መግለጫ Press Release
- kambattomai
- Jan 26, 2024
- 2 min read
ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. (Jan 25, 2024)
ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽል ፎረም (KAIF) የከምባታ ባህል ከጥንት እስከ ዛሬ መጽሐፍ እሁድ ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም. (January 21, 2024) በአዲስ አበባ ብሉ ስካይ ሆቴል ተመርቆ ገበያ ላይ በመዋሉ በቅድሚያ የመጽሃፉን ደራሲና ባለቤት አቶ ሃይሌ ማጊቾ ሴንደኖን፤ ቀጥሎም መላውን የከምባታ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።
ከምባቶማ ኢንተርናሽናል ለመጽሃፉ ህትመት ገንዘብ ለማሰባሰብ (fund raising) በሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. (ጁላይ 8, 2023) ባደረገው ጥሪ መሠረት የድርጊት ጥሪውን ተቀብለው መረጃውን በማሰራጨት ለተሳተፉ ሀብታቸውን በልግስና ለሰጡ ግለሰቦች እና ቡድኖች ከልብ እናመሰግናለን።
በአጭሩ የአቶ ሃይሌን መጽሃፍ ለህትመት ለማብቃት ከምባቶማ ኢንተርናሽናል ካደረጋቸው በርካታ ጥረቶች መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ :
ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. (ጁን 26, 2021) የከምባቶማ ኢንተርናሽናል ፎረም ባካሄደው አለም አቀፍ የአባላትና ደጋፊዎች የዙም ስብሰባ አቶ ሃይሌ ማጊቾን ስለከምባታ ባህልና ታሪክ እንዲገልጹ በክብር እንግድነት ተጋበዙ (እሳቸውን ስንጋብዝ ለመጽሃፉ የምናውቀው ነገር አልነበረም)። ስለከምባታ ባህልና ታሪክ ያዘጋጁትን ትምህርታዊ መልዕክት ካቀረቡ በኋላ በነበረው የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ከዛሬ 4 እና 5 አመታት በፊት አንድ መጽሃፍ ጽፌ ለማሳተም ቢሞክር ብዙ ገንዘብ ስለጠየቁኝ፤ ማሳተም ሳልችል ቀርቼአለሁ፤ መጽሃፉም እንዲሁ ተቀምጧል አሉ። መጽሃፍ በመጻፋቸው አመስግነን የተቻለንን ለማድረግ እንሞክራለን የሚል ቃል ሰጥተን ተለያየን። (የዚህን ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በድርጅታችን የዋትስ አፕና የፌስቡክ ገጾቻችን በይፋ ማየት ይቻላል)።
የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ቦርድም መፅሐፉ ለቀጣዩ ትውልድ የማህበረሰቡን ባህልና ወግ ለማስጠበቅ ያለውን አስተዋፅኦዎች ከተወያየን በኋላ በጉዳዩ ላይ ወደፊት ለመግፋት ወሰንን፣ እስከዚያው ድረስ ስለመጽሃፉ ምንነትና ይዘት በቅድሚያ ለመገምገም የክቡር ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሰኖን የሙያ ድጋፍ ጠየቅን. በዚህ መስረት መጽሃፉን ረቂቅ አይተው የበኩላቸውን ጠቃሚ አስተያየት ለአቶ ሃይሌ ሰጥተወል. በተጨማሪም መጽሃፉን የገመገሙበትን ሪፖርት ለከምባቶማ ኢንተርናሽናል ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. (May 3, 2023) በላኩት ኢሜይል ገልጸውልናል።
• ሪፖርትን ከተመለከትን በኋላ መጽሃፉ ታትሞ መውጣት እንዳለበት ወስነን፤ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥሪ ለመላው የከምባታ ተወላጆች እንዲቀርብ፤ እንዲሁም በአሜሪካ ሀገር የሚሰበሰበው ገንዘብ በከምባቶማ ኢንተርናሽናል የባንክ አካውንት እንዲገባ፤ በኢትዮጵያና በሌሎች ሀገሮች የሚገኙ ወገኖች የሚሰጡት ገንዘብ የሚገባበት አካውንት በአቶ ሃይሌ ማግቾ ስም እንዲከፈት ተማምነን ይህንኑ ለአቶ ሃይሌ አሳውቅን።
ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. (ጁላይ 8, 2023) የከምባቶማ ኢንተርናሽናል የገንዘብ ማሰባሰብ (fund raising) ጥሪ ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የዞኑ ተወላጆች አቀረበ። ይህን ጥሪ ተከትሎ የከምባታ ተወላጆች ያደረጉት ርብርብ የሚደነቅ ነበር። ግለሰቦችና በርካታ የሶሻል ሚዲያ ግሩፖች ሼር በማድረግ መልዕከቱ ለብዙዎች እንዲዳረስ አድርገዋል። አበረታች አስተያየቶችን በመስጠት ብዙዎችን አነሳስተዋል። ከሁሉም በላይ ገንዘባቸውን ሳይሰስቱ ለግሰዋል።
በዚህም የተነሳ 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከጠበቅነው በላይ ገንዘብ ተሰብሰቧል። በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የተሰበሰበውን ገንዘብ ከምባቶማ ኢንተርናሽናል መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ሴፕተምበር 25, 2023) ለአቶ ሃይሌ ማግቾ ማስተላለፉን በይፋ አስታወቀ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጥቂት ወራት ውስጥ የመጽሃፉ ሕትመት ተጠናቅቆ ለንባብ ቀርቧል። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ጥረቱን ማጠናቀቃችንና ፍሬያማ መሆናችን በማህበረሰባችን ትብብር በጣም እንድንኮራ አድርጎናል።
ይህም “ሜጦማት መቆሃ” የሚለውን የከምባታ ማህበረሰብ በጋራ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልና ወግ ውጤታማነት በተጨባጭ አሳይቶናል።
ለተወሰኑ አመታት በዘለቀው የዚህ መጽሃፍ ህትመት ሂደት የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የበኩሉን አሻራ በማሳረፉ ደስታ ቢሰማውም፤ ፎረሙ ያቀረበላቸውን ጥሪ ሰምተው ሳያመነቱ ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን አውጥተው ለለገሱ ወገኖች በሙሉ ከፍ ያለ ደስታና ኩራት እንደሚገባቸው በማመን “እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን”
ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. (ጃንዌሪ 25, 2024)
Comments