top of page
Search

37ኛው የከምባቶማ ኢንተርናሽናል ፎረም/ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ፌብሪዋሪ 13 ቀን 2021 ዓ ም ተካሂዷል።

Writer's picture: kambattomaikambattomai

ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 13 ቀን 2021 የጎጎታ ኬርን የ25ኛ ኢዮቤልዩ ምክንያት በማድረግ የተጋበዙት የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ፕሮፌሰር አክሊሉ አዛዥ ሲሆኑ፤ በስብሰባውም ከኢትዮጵያ፤ ከእንግሊዝ፤ ከታይላንድ፤ ከአውስትራሊያ፤ ከቻይና እና ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተውጣጡ በርካታ የፎረማችን አባላትና የከምባታ ጠምባሮ ክልል ተወላጆች ተካፋይ ሆነዋል።

የፎረሙን መኖር ሳያውቁ የቆዩ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙ ወገኖቻችን እዚህ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ከአሁን ጀምሮ በከምባቶማ ኢንተርናሽናል ፎረም መደበኛ ተሳትፎ እንደሚያደርጉና ለከምባታ እድገትና ልማት የበኩላቸውን ለማድረግ እንድሚጥሩ አስገንዝበዋል። የጉባዔው ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አክሊሉ ለ3ኛ ጊዜ በከምባቶማ ኢንተርናሽናል ፎረም ለመቅረብ ፈቃደኛ ሆነው በፎረማችን ላይ በመገኘታቸው በፎረሙ አባላት ስም አመስግነው ወደ መድረኩ ገብዘዋቸዋል። እሳቸውም ስለ ጎጎታ ኬር አመሠራረት፤ አወቃቀር፤ ዓላማ፤ ራዕይና ክንውኖች በslide ጭምር በስፋት አስረድተዋል። የጉባዔው ተሳታፊዎች ፕሮፌሰር አክሊሉ ለዞኑ ልማትና ዕድገት ሲያበረክቱ ለቆዩትና እያበረከቱ ለሚገኙት የላቀ አስተዋዕጾ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ባቀረቡትም presentation ላይ በርካታ አዎንታዊ አስተያየቶችን አቅርበዋል። የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ፕ/ር አክሊሉ ሁሉንም ጥያቄዎች መልሰዋል። የጎጎታ ኬር እና ከምባቶማ እኢንተርናሽናል ህዝባችንን በሚጠቅሙ ጉዳዮችና ፕሮጀክቶች ዙሪያ collaborate ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። ሁለተኛው አጀንዳ የጎጎታ ኬርን በምን መልኩ/እንዴት መርዳት እንችላለን? የሚል ነበር። ከምባቶማ ኢንተርናሽናል የጎጎታ ኬርን የ25ኛ ኢዮቤልዩ ምክንያት በማድረግ ለጎጎታ ኬር ከአባላትና ደጋፊዎች መዋጮ መሰብሰብ ጀምሮ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተገልጾአል። እዚህ የሚደረገውን መዋጮ ያላወቁ አሜሪክ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በቀጥታ በጎጎታ ኬር አካውንት በኩል ማዋጣታቸው ተነግሮአል።

አውስትራሊያ የሚኖሩ የፎረሙ አባልም በቀጥታ ወደ ጎጎታ ኬር አካውንት ማስገባታቸውንም ገልጸዋል። እስካሁን ያላዋጡ ወገኖች በከምባቶማ ኢንተርናሽናል በኩል እየተካሄደ ባለው የመዋጮ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጓል። ከዚህ አኳያ በማንኛውም የአሜሪካ ግዛት የሚገኙ አባላትና ደጋፊዎች በZelle app የዶ/ር ሃይሌ ቀልብሶን ስልክ ቁጥር (3015123549) በማስገባት በቀጥታ በባንክ አካውንት ውስጥ ማስገባት እንደሚችሉ፤ እንዲሁም የስሜነህ ወልደሰንበትን ስልክ ቁጥር (9175699007.) በማስገባት በCash App እና Venmo በኩል ባንክ ማስገባት እንደሚችሉ ድጋሚ ማሳሳቢያ ተሰጥቷል። በመጨረሻም የከምባቶማ ኢንተርናሽናል የቦርድ አመራሮችንና የሥራ እንቅስቃሴን የሚመለከት አጭር ማሳሳቢያ ለጉባዔው ተገልጾአል። ኡጀቀንቹኔ ምናደብሃት! ሜጦመት መቆሃ ሰላም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ይሁን!

2 views0 comments

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page