top of page
Search

ለከምባታ ዞን ተወላጆች የእርዳታ ጥሪ

  • Writer: kambattomai
    kambattomai
  • Jul 8
  • 1 min read

በሐምባርቾ ተራራ አዲስ እየተሰሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች የሚውል እርዳታ ስለማሰባሰብ

ባለፈው ሳምንት የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አረጋ እሼቱ፤ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ እና ሌሎች የዞኑ ተወላጆች ተገኝተው በሐምባርቾ 777 በሚሰሩ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቀረቡላቸውን ጥያቄዎችም መልሰዋል። ወደፊትም እንደአስፈላጊነቱ ተገኝተው ከዞኑ ተወላጆች ጋር በልማት ጉዳዮች እንደሚመክሩ ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት በሐምባርቾ ተራራ ላይ እየተሰሩ በሚገኙና ሊሰሩ በታቀዱ ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።


ፕሮጀክቶቹ የዞኑን የቱሪዚም ዕድሎችን የሚያሳድጉ፤ የዞኑን ገጽታ የሚያሻሽሉና ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተጣምረው የአካባቢውን ምጣኔ የሚያሳድጉ እንደመሆናቸው መጠን የዞኑ ተወላጆች በገንዘብ፤ በዕውቀትና በሚችሉት ሁሉ የበኩላቸውን ተሳትፎና አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል።


የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የዞኑ ተወላጆች በአካባቢ ልማትና እድገት ጉዳዮች በንቃት እንዲሳተፉ ያበረታታል። ሲያበረታታም ኖሯል። አሁንም ሆነ ወደፊት የበኩሉን አስተዋጽኦ ከማድረግ ወድኋላ አይልም።


አሁን በሐምባርቾ 777 ደረጃዎችና በሐምባርቾ ተራራ እየተሰሩ የሚገኙና ሊሠሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶች የሁላችንንም እገዛና ተሳትፎ የሚሹ በመሆናቸው የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም በውጭ ሀገራት ነዋሪ የሆኑ የዞኑ ተወላጆች የበኩላቸውን እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል።


የተለገሰው ገንዘብ አንዳች ሳይጎድል ለዞኑ በማድረስ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚያደርግ መሆኑን እያረጋግጥን፤ የገንዘብ እርዳታችሁን ከዚህ በታች ባሉት የመክፈያ መንገዶች ከዛሬ ጀምሮ እንድትለግሱ በአክብሮት እንጋብዛለን። ገንዘቡ እንደተለገሰ በአካውንታችን ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ የምስጋናና የማረጋገጫ መልዕክት ለእያንዳንዱ ለጋሽ በገንዘብ ያዣችን በአይናለም ማርቆስ በኩል እንዲርስ የሚደረግ መሆኑንም በአክብሮት እንገልጻለን።


Kambattoma Action International Form Wells Fargo Bank

Zelle:- 850-264-2876

CashApp፡- $AyneMarkos


ሜጦመት ማቆሃ! ሜጦማን አብናም!

ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ሐምሌ 1, 2017 ዓ.ም. July 8, 2025


 
 
 

Recent Posts

See All
KAIF - KMG Ethiopia Partnership

ለዉድ ወገኖቻችንና ደጋፊዎቻችን በሙሉ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም (Kambattoma Action International Forum/KAIF) ከ KMG Ethiopia ጋር አብሮ...

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page