የጎጎታ ኬርን 25ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ከአባላቱና ደጋፊዎቹ $4,750 ዶላር አሰባስቦ እንደነበር ይታወቃል።
ገንዘቡን ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑ ሕጋዊና ሌሎች የአሰራር ደንቦች ተጠናቅቀው የተሰበሰበዉ ገንዘብ ኖቬምበር 5, 2021 ዱራሜ ወደሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጎጎታ ኬር አካውንት ተላልፏል። ከ$4750 ዉስጥ $45.00 ገንዘቡን ላስተላለፈው ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ተቆርጦ ቀሪው $4,705.00 ዶላር ለጎጎታ ኬር ተላልፏል። በደረሰኞቹ ላይ የተደለዘዉ ገንዘቡን ያስተላለፈችው የከምባቶማ ገንዘብ ያዥ (treasurer) የግል ኢንፎርሜሽን ነው። የተላከዉ ገንዘብ በዞኑ አካባቢዎች ለሚገኙ ት/ቤቶች የReference መፅሃፍት መግዣ እንደሚውል ከጎጎታ ኬር አመራር ጋር የተወያየን ሲሆን 7ቱም ት/ቤቶች ተለይተው ታውቀዋል። ገንዘቡን ለለገሳችሁ ወገኖች በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ከሁሉም በላይ ሕዝባችን ያመሰግናችኋል። ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም።
Comments