ጎጎታ ኬር ከከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ጋር በመተባበር #ከ2 መቶ ሀያ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ በዞኑ ዉስጥ ለሚገኙ 8 ት/ቤቶች በዛሬዉ እለት ከ900 በላይ የማጣቀሻ መፅሀፍትና 112 የቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ።
ታህሳስ 21/2014 ዓ.ም ጎጎታ ኬር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ህዝቦች ልማት ማህበር ከከምባቶማ አክሽን አለምአቀፍ ፎረም ጋር በመተባበር ከ2 መቶ ሀያ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ለጉልባና፣ ሆዶ፣ ጆሬ፣ ሰረራ፣ ፋንዲዴ፣ አመለቃና ሆሌገባ ዛቶ 2ኛ/ደ/ ት/ቤቶች ከ900 በላይ የማጣቀሻ መፅሀፍትና ለቃጫ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ደግሞ 112 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ድጋፍ አድርጓል።
የጎጎታ ኬር ዋና ዳይሬክተር አቶ አብነት ወትሮ እና የዞኑ የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አምባዬ አበራ የአጋዥ መፅሀፍቱን ለት/ቤቶቹ ርዕሰ መምህራን አስረክበዋል።
የጎጎታ ኬር ዋና ዳይሬክተር አቶ አብነት ወትሮ ድጋፉን አጠናክሮ በማስቀጠል ትምህርት ቤቶች ላይ ያለዉን የማጣቀሻ መፅሀፍት እጥረት የመቅረፍና ላይብረሪዎችን የማደራጀት ስራ በቀጣይ ዙሮችም እንደሚከናወን ገልፀዋል።
በርክክቡ ወቅት የልማት ማህበሩ የትምህርት ልማት ዘርፍ አስተባባሪና ድጋፍ የተደረገላቸዉ ት/ቤቶች ር/መምህራን ተገኝተዋል።
ድጋፉ የተደረገላቸዉ ስምንቱ ትምህርት ቤቶቹ በዞኑ ውስጥ በ8 የገጠር ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ስለተደረገዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
Comments