ውድ የከምባቶማ አክሽን ዓለምአቀፍ ድርጅት (ፎረም) አባላት በሙሉ፣ ደጋፊዎች፣ ወዳጆች፣ መላው የከምባታና የሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ፥ ከምባቶማ አክሽን ዓለም አቀፍ ድርጅት እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ ይላል።
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የደስታ፣ አብሮነትና መቻቻል የሚታይበት፣ መልካም ዕሴቶቻችን የሚለመልሙበት፣ ኋላ ቀርነት፣ ድህነት፣ መከራ፣ ችግር፣ ረሃብና ጦርነት የሚቀረፉበት፣ ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚገባበት፣ ሌብነት፣ ሙስና፣ ዝርፊያ የሚያበቃበት፣ እሾክና አሜከላ የሚነቀልበት፣ በሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና የሚታይበት፣ የልማት ማነቆዎች የሚወገዱበት፣ አንድነትና እኩልነት ተዘርቶ የሚታጨድበት፣ የሚያድጉበት፣ በውጤቶቻቸውም እንደ ሕዝብ የምንገለገልበት፣ የምንለወጥበትና የምናድግበት እንዲሆን ከምባቶማ አክሽን ዓለም አቀፍ ድርጅት (ፎረም) ይመኛል።
መልካም 2016 አዲስ ዓመት ይሁንልን!
September 11, 2023
Comentarios