የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል አባላት፤ ደጋፊዎችና የዞናችን ተወላጆች በሙሉ እንኳን ደስ አለን።
አቶ ኃይለ ዳንዔል ማግቾ ስለ ከምባታ ባህልና ታሪክ የሚገልጽ መጽሃፍ ከጻፉ በኋላ በማሳተሚያ ገንዘብ እጥረት የተነሳ መጽሃፉን ሳያሳትሙት ለረዥም ጊዜ መቆየታቸውን ድርጅታችን ከሰማ በኋላ ይህን መጽሃፍ ለማሳተም የሚያችስል ገንዘብ ለመሰብሰብ ከጥቂት ወራት በፊት ለዞናችን ተወላጆች በሙሉ ጥሪ አድርገን እንቅስቃሴ መጀመራችን ይታወሳል።
ጥሪውን ያደረግነው 'ሜጦመት መቆሃኔ' በሚለው የከምባታ የትብብር መርህ ላይ ተመርኩዘን በጋራ ከተንቀሳቀስን ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንችላለን በሚል እምነት ነበር።
እነሆ ያ እምነታችን አሁን ተግባራዊ ሆኗል። ያሰብነውም ተሳክቷል።
ለአቶ ኃይለ ዳንዔል ማግቾ መጽሃፍ፡
አሜሪካ ከሚገኙ የዞኑ ተወላጆች 320, 544.00 ብር፤ በአቶ ኃይሌ ማግቾ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ከኢትዮጵያና ሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ የከምባታ ተወላጆች 301, 000. 00 ብር በድምሩ 621, 544.00 ተሰብስቧል። ከውጭም ከኢትዮጵያም የተሰበሰበው 621, 544 ብር በሙሉ ለአቶ ኃይሌ ዳንዔል ማግቾ መድረሱን አረጋግጠውልናል።
በለገሳችሁት ገንዘብ መጽሃፉ በቅርቡ ታትሞ እንደሚወጣና የከምባታን ባህል፤ ወግና ታሪክ ለማጉላት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት እምነታችን ነው። ገንዘብ የለገሳችሁ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርካችሁ። ኮርተንባችኋል። ገንዘቡን በማሰባሰብ ሂደት አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ሁሉ ለመጥቀስ ባንችልም፤ አቶ አዲሴ ጋርካቦና አቶ ፋንታሁን በላይነህ የመዋጮው ጥሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ለብዙዎች እንድደርስ ላደረጉት ጥረት ምስጋናችን የላቀ ነው። ከአሜሪካ ገንዘብ የለገሳችሁ ወገኖች በሙሉ ስማችሁንና የሰጣችሁትን የገንዘብ መጠን የሚገልጽ ደረሰኝ (Receipt) በግላችሁ እንዲደርስ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
በቅርቡ የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም በሚያዘጋጀው የኦንላይን ስብሰባ አቶ ኃይለ ዳንዔል ማግቾ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የሚገኙ መሆናቸውንና በከምባታ ባህልና ታሪክ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት የሚደረግ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እየገለጽን፤ ሁላችሁም በያላችሁበት ሆናችሁ በስብሰባው እንደምትካፈሉ ተስፋ እናደርጋለን።
የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም። ሜጦማት ማቆሃኔ። ዳንዴናም። ሴፕተምበር 25, 2023።
See insights and ads
Boost post
Like
Comment
Share
Kommentare