የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ስብሰባውን ስከፍቱ የዛሬውን ስብሰባ ልዩ የሚያደርገው እስከዛሬ ድረስ ስንሰራ የነበረው ፍሬ ያፈራበት ተጨባጭ ውጤት ይዘን የመጣንበት በመሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል። በማያያዝም የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም በአሜሪካ ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ካገኘ ወራት ያስቆጠረ ቢሆንም የባንክ አካውንት ለመክፋት የሚያስፈልጉ በርካታ መሥፈርቶችን አሟልቶ በድርጅቱ ስም የባንክ አካውንት መከፈቱን ይፋ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ የድርጅቱ ሎጎና ዌብ ሳይት ተሰርቶ ማለቁና የማሻሻያ ሃሳቦችና አስተያየቶች ካሉ ለመቀበል ዛሬ ለጉባኤው ተሳታፊ አባላት ይፋ የሚደረግ መሆኑን ገለጻዋል። በማያያዝም የዕለቱን አጀንዳዎች አስታውቀው መድረኩን ለውይይት ከፍተዋል።
አጃንዳ 1 የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ሎጎና ዌብሳይት ነው።
ዕጩ ዶ/ር ሰላሙ ስለዌብሳይቱና ሎጎው ዲዛይን ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ የዌብሳይቱን እያንዳንዱን ክፍል ይዘት እያሳዩ በስፋት አስረድተዋል። ተሰብሳቢዎች በዌብሳይቱ ዲዛይንና ፕሮግራምንግ ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አመስግ ነዋል። መሻሻል ይኖርባቸዋል ያሏቸውንም አስተያየቶች ሰጥተዋል። የተሰጡትን አስተያየቶች ተቀብለው ማሻሻያ አድርገው ሥራውን አጠናቀው በቅርቡ እንደሚያቀርቡም ገልጸዋል።
አጀንዳ 2 የአባልነት መዋጮና ምዝገባን የሚመለከት ነበር። ይህን በተመከተ ከዚህ በፊት
የአባልነት ምዝገባና መዋጮ ፎርም እንዲያዘጋጁ የተሰየሙት ሁለት አባላት አጠናቅቀው ያቀረቡት የአባልነት ፎርም በዌብሳይቱ እንዲጫን ተወስኗል። የአባልነት እርክኖች የወርሃዊ መዋጮ መጠንና የተለያዩ ዓይነት የአባልነትና የመዋጮ እርከኖችም ከዚህ በፊት በተሰየመው የሁለት አባላት ኮሚቴ ተሰርቶ ያለቀ ስለሆነ ከዚህ ከሴፕተምበር ጀምሮ ወርሃዊ መዋጮ መክፈል መጀመር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። መዋጮውን እንደምርጫችን የ6 ወሩን ወይም የአንድ ዓመቱን በአንዴ አሊያም በየወሩ መከፈል የሚቻል መሆኑ ተገልጿል። አጃንዳ 3 የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የባንክ አካውንትና አካውንቱን መጠቀም ስለመጀመር ነበር።
ስለአካውንቱና አካውንቱን በመክፈት ሂደት ስለተከናወኑ ጉዳዮች የየድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ማብራሪያ ለመስጠት በተቃረቡበት ወቅት የኦንላይን ግንኙነት መስመር በመቋረጡ ሳይሆን ቀርቷል። ይሁንና የተቀሩት አባላት በአጀንዳው ውይይታቸውን ቀጥለው ከዚህ በፊት የጎጎታ ኬር የተመሰረተበትን የ25ኛ ዓመት ኢዮቤሊዩ ሲያከብር የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም ከአባላቱ ያሰባሰበው $4750.00 የአሜሪካ ዶላር በአባላችን የግል የባንክ አካውንት እንደተቀመጠና ይህ ገንዘብ አሁን ወደ ድርጅቱ የባንክ አካውንት ተዛውሮ ወደ ጎጎታ ኬር የሚላከበት ሂደት እንዲጀመር ተወስኗል። የተሰበሰውን ገንዘብ በግል አካውንታቸው በአደራ ያስቀመጡ አባል ገንዘቡን ሰሞኑን እንደሚያስተላልፉ አስረድተዋል። ሌላው ከዚህ አጀንዳ ጋር አብሮ የተነሳው ለማስተር አብነት ከበደ ሞተር ብስክሌት ለመግዛት በማሰብ አንዳንድ ግለሰቦች በጎፈንዲሚ አካውንት ከፍተው ያሰባሰቡት ገንዘብ ጉዳይ ነበር። ለማስተር አብነት ሞተር ብስክሌት መግዣ በማሰባሰቡ ሂደት ላይ የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም እጅ የሌለ መሆኑንና በጥቂት ግለሰቦች ተነሳሽነት የተከነወነ መሆኑ ተጠቅሷል። ነገር ግን የተሰበሰበው ገንዘብ በግልጽነት ለተፈለገው ዓላም እንዲውል ለማስቻል ገንዘቡ ከጎፈንድሚ ወደ ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ባንክ አካውንት እንዲዛወር የማድረጉ ሂደት እንዲጀመር ማድረጋቸውን ምናልባትም በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከጎፋንድሚ መሉ በሙሉ እንደሚተላለፍ ገንዘብ ያዧ ገልጸዋል። ለማስተር አብነት ለማስረከብ የሚረዱ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አመራር አካላትን የመገናኘትና የማስተባባር ሥራ እንዲጀመርም ሃሰብ ቀርቧል።
የመጨረሻው አጀንዳ አቶ ሃይሌ ማግቾ ስለ ከምባታና ጠምባሮ ሕዝቦች ባህልና ታሪክ የሚገልጽ መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ ማሳተም አቅቷቸው እስካሁን ድረስ ስለተቀመጠው መጽሐፍ ጉዳይ ነበር።
አቶ ሃይሌ ከ3 የመጽሐፍት አሳታሚ ድርጅቶች አውጥተው ፕርፎርማዎችን መላካቸውንና 3ሺ ኮፕ ለማሳተም በትንሹ 300,000 ብር እንደሚያስፈልግ ሰብሳቢው አስረድተዋል። በዚህ ጉዳይ አስተያየት የሰጡ አባላት የዞኑን የልማት ማህበር ጨምሮ ሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች ይህ መጽሐፍ እንዲታተም የበኩላቸውን አስተዋዕጽኦና ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል። አክለውም ብዙ ጊዜ መጽሐፍት ሲታተሙ ለመጀመሪያ ጊዜ አነስተኛ ኮፒ እንደሚታተምና ገበያውና ተፈላጊነቱ እየታየ 2ኛና 3ኛ ህትመት እንደሚካሄድ ጠቁመው፤ አቶ ሃይሌም ከ3ሺ ይልቅ በ1ሺ ወይም በ500 ኮፒ ለማሳተም ምን ያህል እንደሚፈጅ ሌላ ፔርፎርማ እንዲያቀርቡ ቢደረግ ይሻላል የሚል ሃሳብ አቀርበው ሰበሳቢው ይህንኑ ለአቶ ሃይሌ ማግቾ እንደሚያደርሱ ገልጸዋል። በዚሁም የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።
ኡጀቀንቹኔ ምናደብሃት። ሜጦመት መቆሃ!
ሰላም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ይሁን!
Comments