ለከምባታ ጠምባሮ ተወላጆችና ወዳጆች የቀረበ የድጋፍ ጥሪ። በአስተማሪነት፤ በአስተዳዳሪነት፡ በሽማግሌነትና የከምባታን ወግና ባህል በመተረክ የሚታወቁት የከምባታ ተወላጅ አቶ ሃይሌ ማግቾ የከምባታ ባህል፡ ከጥንት እስከ ዛሬ የሚል ድንቅ መጽሃፍ ጽፈው ካዘጋጁ በኋላ መጽሃፉን ለማሳተም አቅም አጥተው ለረጅም ጊዜ በመቆየታቸው ለመጽሃፉ ሕትመት የሚሆን የገንዘብ እርዳታ እንድደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የተጻፈውን መጽሃፍ ይዘትና ምንነት የከምባታ ምሁራን ተመልክተው ሃሳብ ቢያቀርቡ የተሻለ ይሆናል በሚል እምነት ከምሁራኖቻችን መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነቶች ረዳት ፕሮፌሰር ለሆኑት ለፕ/ር ያዕቆብ አርሰኖ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
ፕ/ር ያዕቆብ ጥያቄአችንን ተቀብለውና ካላቸው የተጣበበ ጊዜ ወስደው የመጽሃፉን ረቂቅ አንብበው መጽሃፉ የከምባታ ባህል እና የከምባታ ታሪክ ተብሎ በ2 ክፍሎች ቢከፈልና የከምባታ ባህል የሚለው 1ኛ መጽሃፍ አስቀድሞ ቢታተም፤ ከዚያ ቀጥሎ መጠነኛ እርምት ተደርጎበት የከምባታ ታሪክ የሚለው 2ኛ መጽሃፍ ቢታተም የሚል ሃሳብ አቅርበው አቶ ኃይሌ ሃሳቡን በደስታ መቀበላቸው ተገልጾልናል።
ፕሮፌሰር ያዕቆብ ስለመጽሃፉ ከሰጡት የግምገማ አስተያየት መከካል የሚከተለው ይገኛል። “In my opinion: 1. The manuscript is a highly valuable contribution in view of recording and preserving Kambata intangible cultural heritage. 2. When published, the book will be useful as source material for scholars and academic researchers who may be interested in Kambata study. 3. The book will serve as firsthand knowledge about the rich cultural heritage and overall life of the Kambata society. 4. The book will provide an introductory impression to visitors from outside. 5. The book will help build the knowledge of younger and successive generations of Kambata about their own society.” ከዚህ በመነሳት የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም መጽሃፉ ቢታተም የከምባታን ባህልና ማንነት በማሳወቅና በማሳደግ ረገድ የሚያበረከተው ድርሻ የላቀ እንደሚሆን ያምናል። ስለሆነም ለህትመቱ የሚሆን ገንዘብ ከሀገር ውጭና ሀገር ውስጥ ከሚገኙ የዞኑ ተወላጆችና ወዳጆች ለመሰብሰብ ወስነን ስለተነሳን እያንዳንዳችሁ የተቻላችሁን ሁሉ እንድታደርጉ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በአሜሪክ ግዛቶች የምትኖሩ ወገኖቻችን ለዶ/ር ሃይሌ ገዕኖሬ ቀልቢሶ በZelle (ስልክ ቁጥር 301 512 3549) መላክ ትችላላችሁ። ለአቶ ሰለሞን ዲፋሴ ባሶሬ Zelle እና CashApp (ስልክ ቁጥር 614 804 1274) ድጋፋችሁን መላክ ትችላላችሁ። በኢትዮጵያ የምትገኙ የከምባታ ጠምባሮ ተወላጆችና ወዳጆች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአቶ ሃይሌ ማግቾ አካውንት ቁጥር 1000038809397 በማስገባት ድጋፋችሁን እንድታሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። በደቡብ አፍሪካ፤ አውስትራሊያ፤ አውሮፓና በሌሎች የውጭ ሀገራት የምትኖሩ ወገኖቻችን በአቶ ሃይሌ ማግቾ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000038809397 ድጋፋችሁን መላክ ትችላላችሁ።
የሚሰበሰበውን የገንዘብ ድጋፍ እየተከታተልን በከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የዋትስአፕና የፌስቡክ ገጾቻችን የምናሳውቅ መሆናችንን እየገለጽን ይህንን መጽሃፍ በማሳተም አብረን ታሪክ እንድንሰራ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ደንዴናም!!!
Comments