Kambattoma Action International Forum (KAIF) would proudly like to congratulate our brother Dr. Deginet Wotango on his PhD graduation in Law & Language from the University of Cologne (Universitat zu Koln), “one of the most prestigious and research-intensive universities in Germany.”
Dr. Deginet completed the high school in Durame Senior Seconday School. He graduated with a Bachelor of Law Degree from Addis Ababa University & got his MA in Comparative Public Law & Good Governance. He also studied Project Management & Planning; and Leadership & Civic Engagement in various institutions. He worked as a university lecturer, served as a Public Prosecutor, & also practiced as a Private Attorney & Legal Consultant.
Dr. Deginet’s thesis in the Ethiopian Official Multilingualism Use & Multilingual Law-Making also investigates the European Union Multilingualism Use & the challenges and opportunities involved in the multi-lingual law-making process. This, we believe, will be ground-breaking research, the findings of which will immensely benefit Ethiopia, a multi-lingual & multi-cultural nation with official multilingualism ad federal system of government.
We believe Dr. Deginet Wotango’s academic knowledge and professional contributions to Ethiopia in crafting & implementation of multilingual laws will be great. Congratulations again! KAIF July 7, 2023 ወንድማችን ዶክተር ደግነት ዎተንጎ በጀርመን ሀገር ከሚገኘው ከተዋቂው University of Cologne (Universitat zu Koln) በቋንቋና ሕግ (Law & Language) የጥናት ዘርፍ በዶክትሬት (PhD) ዲግሪ በመመረቁ የከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም የተሰማዉን ከፍተኛ ደስታ በኩራት እየገለፀ፣ ዶ/ር ደግነትን፤ ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹንና መላዉን ሕዝባችንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።
በዱራሜ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ዶ/ር ደግነት የባችለር ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት (LLB) ያገኘ ሲሆን፤ የሁለተኛ (ማስትሬት) ዲግሪውን ደግሞ በ Comparative Public Law & Good Governance ሰርቷል። ከዚህ በተጨማሪ ስለ ፕሮጀክት አመራርና እቅድ፤ እንዲሁም ስለ አመራርና ሲቪክ እንጌጅመንት በተለያዩ ተቋሞች ተምሯል። ሀገር ውስጥ በነበረበት ወቅት የዩኒቨርሲቲ አስተማሪነት (Lecturer) እና አቃቤ ህግ ሆኖ አገልግሏል።
ዶ/ር ደግነት አሁን በ PhD የተመረቀበት የሕግ እና የቋንቋ የጥናት ዘርፍ በተለይም እሱ የመመረቂያ ጥናቱን የሰራበት የኢትዮጵያን ኦፊሻል ብዘሃቋንቋ አጠቃቀም (Official Multilingualism Use) ከአውሮፓ ሕብረት Multilingualism (ብዘሃ ቋንቋ አጠቃቀም) ጋር በማስተያየትና በማነጻጻር ያካሄደው ጥናት ከብዘሃ ቋንቋ የህግ አወጣጥ (multilingual law making) ጋር ያለውን ተግዳሮቶችና እድሎች አጣምሮ የሚመረምር ነው። የዶ/ር ደግነት የጥናትና ምርምር ዘርፍ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በፌዴራል ሥርዓት ውስጥ ብዝሃ ኦፊሻል ቋንቋዎች ላሏት፤ የቋንቋና የባህል ብዝሃነት ላለባት ፌዴራላዊት ሀገር እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆንና ዶ/ር ደግነት የበኩሉን የሙያዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተስፋ እናደርጋለን። ዶ/ር ደግነት እንኳን በድጋሚ ደስ አለህ። ከምባቶማ አክሽን ኢንተርናሽናል ፎረም። ጁላይ 7, 2023።
Comments